በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውሃ በራስ መሸከም ከባድ የጤና መዛባት ሊያስከትል እንደሚችል አንድ አዲስ የወጣ ጥናት አስታወቀ


በአፍሪካ ሃገሮች ሴቶች እና ልጃገረዶች ለቤተሰባቸው ለምግብና ለሚጠጣ ደግሞም ለመተጣጠቢያ የሚያስፈገውን ውሃ አንዳች በሚያህል እንስራ ወይም ጄሪካን ሙሉ ውሃ ከሩቅ ቦታ ቀድተው በራሳቸው ተሸክመው ይወስዳሉ። አንድ አዲስ ጥናት ታዲያ ይህ ከጥንት ጀምሮ ያለ ስራ የሴቶቹ ጤናና ሌላም ደህንነትቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት መርምሩዋል።

ከወንዝ ሆነ ከምንጭ የሚቀዱት ዉሃ ክብደቱ እስከ አስራ ስምንት ኪሎ ግራም ይደርሳል ። ታዲያ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ታዳጊ ልጃገረዶች ተጋግዘውም ቢሆን በዘዴ አንከብክበው ጭንቅላታቸው ላይ ያደርጉና ሰላሳም አርባ አምስትም ደቂቃ የሚፈጀውን ጉዞ ይያያዙታል።

ጄይ ግራም ዋሽንግተን ዲስ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የአከባቢያዊና የስራ ጤና ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። እሳቸውና ባልደረቦቻቸው በህዝብ ጤና ጥበቃ ዙሪያ ለሚያካሂዱት ምርምራቸው ነው የውሃ አቀዳዱን ልማድ ጥናት ያደረጉበት ።

“ውሃውን እንዴት ነው የሚቀዱት ከየት ነው የሚያገኙት የሚለውን ብዙ ትኩረት ሰጥተናዋል። ይህን ለምን እንዳደረግን መቼም ግልጽ ነው። ምክንያቱም ውሃውን የሚቀዱት ከወንዝ ፡ ከምንጭ ወይም ከሃይቅ ከሆነ ያው የተበከለ ውሃ እንደሚሆን እናውቃለን። ስለዚህ ህዝብን ጥራቱ የተጠበቀ ውሃ ወደሚያገኙበት ሁናቴ ማሸጋገር የሚቻለው እንዴት ነው የሚለው ብዙ ትኩረት ተሰጥቶታል።” ብለዋል

በታዳጊ ሀገሮች ለማህበረሰቦች የውሃ አቅርቦትን እና ንጽህናውን ማሻሻል በጤና ፡ በተመጣጠነ ምግብ እና በትምህርት ዘርፎች መጠነ ሰፊ ጠቃሚ ውጤት እንደሚኖረው ጥናቱ ያስገነዝባል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ውሃ በራስ መሸከም ከባድ የጤና መዛባት ሊያስከትል እንደሚችል አንድ አዲስ የወጣ ጥናት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG