በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ የሠላሳ ሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፋ


ቤንጋዚ ሊቢያ
ቤንጋዚ ሊቢያ

በሰሜን ምሥራቃዊቱ የሊቢያ ከተማ ቤንጋዚ በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ የተጠመዱ የቦምቦች ፈንድተው ለሠላሳ ሦስት ሠዎች ሕይወት መጥፋት እና ሌሎች በርካቶች መቁሰል ምክኒያት መሆናቸው ተገለጠ።

በሰሜን ምሥራቃዊቱ የሊቢያ ከተማ ቤንጋዚ በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ የተጠመዱ የቦምቦች ፈንድተው ለሠላሳ ሦስት ሠዎች ሕይወት መጥፋት እና ሌሎች በርካቶች መቁሰል ምክኒያት መሆናቸው ተገለጠ።

በትላንትናው ዕለት የደረሱት መንትዮቹ የቦምብ ጥቃቶች፤ የመጀመሪያው አል-ሳልማኒ መንደር ከደረሰ ሠላሳ ደቂቃዎች በኋላ የፈነዳው ሌላ ቦምብ ደግሞ በጥቃቱ የተጎዱትን ለመታደግ ከሥፍራው የደረሱ ፖሊሶችና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ላይ የተነጣጠረ ቦምብ ነው።

ለጥቃቱ ፈጥኖ ኃላፊነት የወሰደ ወገን የለም።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊቢያ ልዑክ፤ በሲቪሊያን ላይ የተነጣጠረው ይህ ጥቃት ዓለምቀፍ የሰብዓዊነት ድንጋጌዎችን ሁሉ የተላለፈ ነው፤ ሲል በጥብቅ አውግዟል።

በፅንፈኛ ኃይሎች እና በሊቢያው የወታደራዊ አንጃ መሪ ፊልድ ማርሻል ካሊፋ ሃፍተር ታማኝ ኃይሎች መካከል በተካሄዱ ውጊያዎች ለሦስት ዓመታት ጦርነት ያልተለያት ቤንጋዚ ባለፈው ዓመት ነው ነፃ ወጥታለች ሲሉ ሃፍተር ያወጁት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG