በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካናዳ የጸረ ኮቪድ ህግጋት ተቃዋሚዎች አመጽ አላቆመም


በመቶዎች የሚቆጠሩት ከባድ የጭነት መኪኖች አሽከርካሪዎች ሰልፍ አካሂደዋል
በመቶዎች የሚቆጠሩት ከባድ የጭነት መኪኖች አሽከርካሪዎች ሰልፍ አካሂደዋል

በዋና ከተማይቱ ኦታዋ ሁለቱን የተቃውሞው መሪዎች በቁጥጥር ስር ያዋለው ፖሊስ የሃገሪቱን የጸረ ኮቪድ ገደቦች በመቃወም ለሦስት ሳምንታት የሚጠጋ ጊዜ የተካሄደውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመበተን ቢዝትም፣ ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶችን የዘጉት በመቶዎች የሚቆጠሩት ከባድ የጭነት መኪኖች አሽከርካሪዎች በትናንትናው ዕለትም የተሽከርካሪዎቻቸውን ጥሩምባ እየነፉ በአመጹ መቀጠል መርጠዋል።

መኮንኖች ያሳፈሩ አውቶቡሶች ወደ አካባቢው እንደደረሱም በኦታዋ ከተቃውሞ አድራጊዎቹ የነበረው ፍጥጫ ይበልጥ እያየለ የመጣ ይመስላል። የከተማይቱ ጊዜያዊ ፖሊስ አዛዥም እርምጃ መውሰዳቸው አይቀሬ መሆኑን ተናግረዋል።

የካናዳ ጨዋነት እና በስፋት የሚታወቅ ህግን የመከተል መልካም ስም የለወጠ የሚመስለው የተቃውሞ ሰልፍ ለሦስት ሳምንታት ያህል ባልተቋረጠውና በከባድ መኪኖች የተካሄደው የአመጽ እንቅስቃሴ የከተማይቱ የወትሮ ሰላማዊ ይዞታ አናውጦ ሰንብቷል። ከበቡ። ፖሊስ ታማራ ሊች እና ክሪስ ባርበር የተባሉትን ከአመጹ አስተባባሪዎች ሁለቱን በቁጥጥር ስር አውሏል። ሆኖም የጸጥታ መኮንኖቹ እስካሁን በኃይል ወደ ተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎቹ አልተንቀሳቀሱም።

XS
SM
MD
LG