በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ጃስቲን ትሩዶ አሸነፉ


የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶ
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶ

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶ ዛሬ በሀገሪቱ በተካሄደ ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፋቸውን ዛሬ ማለዳ አስታውቀዋል። ሊበራል ፓርቲያቸው በገዢ ፓርቲነቱ ለመቀጣል የሚያስችለው በቂ የፓርላማ መቀመጫ አግኝቷል።

የካናዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በዘገበው መሰረት የትሩዶ ሊበራሎች ከምክር ቤቱ 338 መቀመጫዎች 157ቱን ወደ ማሸነፍ አምርተው ነበር። የብዙሃንነት ቦታ ለማግኘት ግን 170 መቀመጫዎች ማግኘት አለባቸው። ስለሆነም ትሩዶ ከተራማጅ አዲስ ዲሞክራቶች ጋር የጥምረት መንግሥት ለመመስረት ይገደዳሉ። አዲስ ዲሞክራቶች 24 መቀመጫዎችን ወደ ማሸነፍ አምርተዋል።

“ካናዳውያን ከጠረፍ እስከ ጠረፍ መከፋፈልንና አሉታዊነትን ወግድ ብለዋል” ሲሉ ትሩዶ ሞንትርየል በሚገኘው ዋናው የምርጫ መሥርያ ቤታቸው ውስጥ ለተሰበስቡ ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል። ተራማጅ አጀንዳንና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጠንካራ ዕርምጃ እንዲወሰድ መርጠዋል ሲሊም ትሩዶ አክለዋል።

በንግድና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ ከትሩዶ ጋር ሲጋጩ የቆዩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በትዊተር እንኳን ደስ ያልዎት ብለዋቸዋል። ካናዳ የሚገባትን አግኝታለች ሲሉም አክለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG