በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ ተወላጅ አህመድ ሁሴን አዲስ የካናዳ ምክር ቤት አባል


አህመድ ሁሴን
አህመድ ሁሴን

አዳዲሶቹ የካናዳ ምክር ቤት አባላት ቃለ-መሓላ እየፈጸሙ መሆናቸው ተሰማ፣ አንዱ ተመራጭ የሶማልያ ተወላጅ መሆናቸውም ተገለጸ።

በ፲፯ ዓመታቸው ወደ ካናዳ የፈለሱትና የሊብራል ፓርቲውን ተወክለው የተወዳደሩት አህመድ ሁሴን፣ በቅርቡ በተካሄደው የአጊቱ የሃገሪቱ ምርጫ፣ ለብዙ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆየውን የወግ-አጣባቂውን ፓርቲ አሸንፈው ነው የተመረጡት።

መመረጣቸውን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ካናዳ የብዙ አገሮች ሕዝቦች ስብጥር የሚገኙባትና፣ የብዙ አገሮች ሕዝቦች ባህል የሚስተናገዱባት አገር መሆኗን ገልጸዋል።

ለምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር ውሳኔ ያደረጉት ባለፈው ዓመት መሆኑን ለቪኦኤ ለአሜሪካ ድምጽ የገለጹት የ፴፱ ዓመቱ ሁሴን፣ ሙስሊም ወይም ስደተኛ መሆናቸውም ለመወዳደር እንዳላስቸገራቸው ተናግረዋል። አዎንታዊ የሆነ የምረጡኝ ዘመቻ እንዳደረጉና አያሌ ደጋፊዎችን ለማግኘትም እንደቻሉ አክለው ተናግረዋል።

መካከለኛ ገቢ ላላቸው የቀረጥ ቅነሳ እንዲደረግ፣ 315,000 ህፃናትን ከድኅነት ቀንበር ማላቀቅ፣ የተመጣጠነ የቤት ኪራይ፣ ለአገሪቱም የተሻለ የህይወት ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ (Infrastructure) እና መንገድ እንዲሰራ የሚሉት፣ በውድድሩ ወቅት ያነሷቸው ዋነኞቹ ነጥቦች ንእደነበሩም አመልክተዋል።

ሕዝብን ከመከፋፈል ይልቅ፣ በሚያስማማው ነጥብ ወደ አንድነት ማምጣት፣ ምርጫን ለማሸነፍ በጣም ጠቃሚ አንደሆነ ተናግረዋል።

የህግ ባለሙያና የማኀረሰብ መብት ተሟጋች የሆኑት አህመድ ሁሴን፣ ካናዳ የሚገኘውን የሶማሌ-ካናዳውያን ምክር ቤት በሊቀ-መንበርነት መምራታቸውም ታውቋል።

የከፍተኛ ደረጃ ወይም ባችለርስ ዲግሪያቸውን (Bachelor's Degree/BA) በታሪክ ከዮርክ ዩኒቨርሲቲ፣ በህግ ደግሞ ፒኤችዲ (PhD) ወይም የዶክተርነት ትምህርታቸውን ከአታዋ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።

ሙሉውን ዝርዝር ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የሶማልያ ተወላጅ አህመድ ሁሴን አዲስ የካናዳ ምክር ቤት አባል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:45 0:00

XS
SM
MD
LG