በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት እንደገና የመኖሪያ ካምፕ አቃጠለ


የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት ቃጠሎ
የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት ቃጠሎ

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያና ኤርትራዊያን ይሠሩበታል በሚባለው በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት ማክመሪ ከተማ ከዐሥራ አምስት ቀናት በፊት የተነሳውን የዱር እሳት በቁጥጥር ስር የዋለ ቢምስልም በትናንትናው ዕለት አቅጣጫውን ወደ ሰሜቱ ክፍል አዙሮ 665 መኖሪያዎች ያሉት የአንድ የነዳጅ ማውጫ ድርጅት አዲስ የመኖሪያ ካምፕ አቃጠለ።

ከዐሥራ አምስት ቀናት በፊት በካናዳይቱ አልበርታ ግዛት ውስጥ የፎርት ማክመሪ ከተማና አካባቢዋ በተነሳ የዱር እሳት ወደ ሰማንያ ሺሕ የሚጠጉ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነገሯቸው ነበር። በዚህም መሠረት በራሳቸው መውጣት የቻሉት በራሳቸው፤ ያልቻሉ ድግሞ በአውሮፕላን እና በሂሊኮፕተር እንዲወጡ ተደርገዋል። በአሁኑ ወቅትም በኤድመንተንና አቅራቢያዋ ባሉ የመጠለያ ቦታዎች ማረፊያ፣ምግብ እና የገንዘብ ድጋፍ እየተሰጣችው ይገኛሉ።

ከከተማው ውጪ ባሉና እሳቱ አይደርስባቸውም ተብሎ በታሰበባቸው የሰሜኑ አቅጣጫ የሚገኙ የነዳጅ ማውጫ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸውን ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመልሱ ተደርገው ነበር። ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ግን እሳቱ በድጋሚ ተነስቶ አንድ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ማውደሙን፣ ወደ ሥራ ተመልሰው የነበሩትን ሰዎችም እንዲወጡ መደረጉን፣ ሰዎችን ከቦታው ለማውጣት በሚደረገው ርብርብ አብሮ እየተሳተፈ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ አቶ ዘላለም መኮንን ገለፆልናል። እርሱም መጀመሪያ እንዲያርፍ ከተደረገበት ኤድመንተን ሰኞ ዕለት እንዲመልስ ሲደረግ ከሥራ ባለደረቦቹ ጋር በእሳት ውስጥ ማለፉን ገልጾልናል።

እንደ አቶ ዘላለም መኮንን ገለፃ በድጋሚ የተነሳው እሳት 665 መኖሪያዎች ያሉት የአንድ የነዳጅ ማውጫ ድርጅት አዲስ የመኖሪያ ካምፕ አቃጥሏል። በከተማው የተነሳውን እሳት መቆጣጠር ቢቻልም በእሳቱ ግን በርካታ ሕንጻዎች ተቃጥለዋል።

የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት ቃጠሎ
የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት ቃጠሎ

እሳቱን ማጥፋት ቢቻል እንኳን መብራት በከተማው እንደሌለ፣ ከቃጠሎ የተረፉት መኖሪያ ቤቶች የቤት ውስጥ የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር እየተነፈሰ ሌላ የእሳት አደጋ ሥጋት እንደሚፈጥር አቶ ዘላለም ገልጾ ከተማውን አቃንቶ፣ ነዋሪዎቹን ወደነበሩበት ለመመለስ እስከ አራት ወር ሊወስድ ይችላል። የሚል ግምት እንዳለው ጠቁሟል። ይህ ደግሞ በድንገት ወጥተው ከእነ ቤተሰቦቻቸው በመጠለያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች ዜጎች ሁኔታውን ከባድ ያደርግባቸዋል ብሏል።

ዘገባውን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ

የፎርት ማክመሪው የዱር እሳት እንደገና የመኖሪያ ካምፕ አቃጠለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG