ዋሺንግተን ዲሲ —
ካሜሩን ከናይጀሪያ ጋር በሚዋስነው ሰሜናዊ ድንበርዋ ላይ፣ ተማሪዎችንና አስተማሪዎችን እየጨመረ ከሄደው የቦኮ ሃራም ጥቃት ለማዳን ስትል፣ ከስልሳ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችን፣ እንደገና እንደዘጋች አስታውቃለች።
የማዕከላዊ አፍሪካይቱ ሃገር፣ ከመኖርያቸው የተፈናቃሉት ተማሪዋች፣ የተሻለ ደኅንነት አለው በሚባል አካባቢ እንዲማሩ፣ ወታደሮች መመደብዋ ታውቋል።
ቦኮ ሃራም የሃገሪቱ ወታደራዊ ኃይል በሚወስደው እርምጃ በመዳከሙ፣ በአጥፍቶ መጥፋት ዘዴ ላይ ማትኮሩ ተዘግቧል።