በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦኮ ሃራም ጥቃት ምክንያት ናይጄሪያውያን ወደ ካሜሩን እየሸሹ ነው


ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ናይጄሪያውያን የቦኮ ሃራምን ጥቃት ሽሽት ባለፉት ሦስት ሳምንታት ከቦርኖ ስቴት ወደ ካሜሩን ዘልቀዋል ተብሏል። በካሜሩን የሚገኙ የስደተኛ መጠለያዎች በመጨናነቃቸው ምክንያት ናይጄሪያውያኑን ለመመገብ ከባድ ሆኗል። የኮሌራ ወረሽኙም ችግሩን አባብሶታል።

የካሜሩን ጦር እንዳስታወቀው ናይጄሪያውያኑ እንደ አዲስ ባገረሸው የቦኮ ሃራም ጥቃት ምክንያት ወደ ካሜሩን ሊሸሹ ችለዋል።

ተፈናቃዮቹ ለቀናት ተጉዘው እንደደረሱና ይኖሩበት በነበሩት መንደሮች የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች ግድያ እየፈጸሙ መሆኑን ተናግረዋል።

ቪኦኤ በቦኮ ሃራም አዲስ ተከፈተ የተባለውን ጥቃት ከገለልተኛ ወገን ማረጋገትት ባይችልም፣ የካሜሩን ባለሥልታናትና ተፍናቃዮቹ በድንበሮች አካባቢ ባለፉት ሦስት ሣምንታት የቦኮ ሃትራ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በካሜሩን ለሚያካሄደው ሰብዓዊ ሥራ እንዲውል ካቀደው 37.8 ሚሊዮን ዶላር 40 በመቶ እጥረት እንዳለበት ገልጿል። ይህም ለናይጄሪያውያኑ ተፈናቃዮች ሊሰጥ የታሰበውን ዕርዳታ ይጨምራል።

የናይጄሪያውያኑ ተፈናቃዮች መከሰት የመጣው፣ በጎርፍ ማጥለቅለቅ ምክንያት የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽን ካሜሩን ለመከላከል በምትታገልበት ወቅት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው፣ በቦኮ ሃራም ጥቃት በተነሳው ግጭት ምክንያት እስከአሁን 36 ሺህ ሰዎች ሲገደሉ፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

XS
SM
MD
LG