በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቦኮ ሃራም የተለያዩ ሁኔታዎች በናይጀሪያና በካመሩን


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የናይጀሪያ መንግሥት በሽብርና ሁከት ቡድኑ ቦኮ ሃራም ላይ ቁልፍ ነው ሊባል የሚችል ድል መቀዳጀቱን ገልጿል፡፡

የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ማማዱ ቡሃሪ ትናንት ባደረጉት ንግግር የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ቡድን ለብዙ ዓመታት ተቆጣጥሮት በቆየው በሳምቢሳ ጫካ ውስጥ ተደምስሰዋል ብለዋል፡፡

ሳምቢሳ በሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ የሚገኝ ዱር ነው፡፡ ከሳምቢሳ ባሻገር ድንበሩን ዘልቆ ግን ተጎራባቾቹ ካመሩናዊያን ሌላ ታሪክ ነው የሚናገሩት፡፡

በትናንትናው የገና በዓል ዕለት ሰሜን ካመሩን ውስጥ ተከታታይ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተዘግቧል፡፡

ይህ ጥቃት ለካመሩንም ለአካባቢውም ጉዳይ ሥጋት የሰነቀ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የካመሩን ሰሜናዊ ክልል አገረ ገዥ ሚዲያዋ ባካሪ አንደሚሉት የአካባቢው የጥበቃ ዘብ ቡድን አባላት አንድ የቦኮ ሃራም አባል ነው የሚባል ተጠርጣሪ ሞተር ቢስክሌት ላይ ሆኖ ክርስቲያኖች ለዕሁድ ፀሎትና አምልኮ ወደሚሰባሰቡበት ከናይጀሪያ ጋር ወደምትዋሰን “ሞራ” የምትባል ከተማ ሲክንፉ አስቁመው ይዘውታል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የቦኮ ሃራም የተለያዩ ሁኔታዎች በናይጀሪያና በካመሩን
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00

XS
SM
MD
LG