በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካምቦድያ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዋናው የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈርስ አዘዘ

የካምቦድያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋናው የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈርስ አዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሀን ሰን ፍፁም ሥልጣንን በበለጠ ለማሰረፅ የተወሰደ እርምጃ ይመስላል።

የካምቦድያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋናው የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈርስ አዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሀን ሰን ፍፁም ሥልጣንን በበለጠ ለማሰረፅ የተወሰደ እርምጃ ይመስላል።

ዘጠኝ ዳኞች የተሰየሙበት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙሉ ድምፅ ያሳለፈው ብይን 118 የካምቦድያ ብሄራዊ መድህን ፓርቲ አባላት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በማንኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳይገቡ አግዷል።

ብሔራዊ መድህን ፓርቲ የሀገሪቱን መንግሥት ለመገልበጥ አሲሯል በሚል የካምቦድይ ገዢ ፓርቲ ያቀረበዋን ክስ ተቃብሎ ነው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የበየነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG