በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

”ለጥያቄዎ መልስ” ከ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ጋር


የጥምረት ለነጻነት ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአድማጮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሰፋ ያለ መልስ ሰጡ

የጥምረት ለነጻነት ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ ጥረት የፈጠሩት ሶስት የፓለቲካ ድርጅቶች ለአንድ ዓመት ያህል በዝርዝር የፓለቲካ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ካደረጉና ካሁን በፊት ከነበሩት የትብብር ሙከራዎች ትምህርት ከቀሰሙ በሁዋላ ነዉ አሉ። ድርጅቶቹ እርሳቸዉ የሚመሩት ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ አፋር ሕዝብ ፓርቲና ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነትና የፍትህ ንቅናቄ ናቸዉ።

ድርጅቶቹ የተስማማባቸዉን ሶስት አንክዋር ነጥበችም እንደሚከተለዉ ዘርዝረዋል።

1. ኢትዮጵያ ዉስጥ ካሁን በሁዋላ የሚፈጠረዉ ሥርዓት፣ ፍጹም ነጻ ከሆነና የሕዝብን ሙሉ ፍላጎት ከሚያንጸባርቅ ምርጫ ዉጭ ምንም ዓይነት የፓለቲካ ሥልጣን ሊኖር እንደማይችልና እንደማይገባ፣

2. ጥምረቱ በአንድ የትግል ስልት ሳይታጠር ሁሉን ዓይነት የትግል ዘዴ በመጠቀም በኢትዮጵያ የፓለቲካ ለዉጥ ለማምጣት፣

3. ወደፊት ዉሳኔ የሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች ላይ በምን መልክ እንደሚወሰን፣ ከሌሎች ድርጅቶችም ጋር በሚኖር የወደፊት ግንኙነት የትግል እስትራቴጂ በጋራ ለመንደፍ ለማስፈጠም መስማማቱን፣

ዶክተር ብርሃኑ ”ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅታችን ላይገልጸዋል። ጥያቄና መልሱን ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG