በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት በአዲስ አበባ ጉዳይ


የፕሮግራሙ ተወያዮች በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካን የተፈጠሮ ሙዚየም የጥናት ቡድን አባል የሆኑት ዶ/ር ዩሃንስ ዘለቀና በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪው የሕግ የፖሊሲና የቢስነስ አማካሪው ዶ/ር ብርሃን መስቀል አበበ ሰኚ ናቸው።

ውይይት በአዲስ አበባ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:38:37 0:00

ለዛሬ ለጥያቄዎ መልስ ለውይይት የተመረጠው ርዕስ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተመራው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ ረቂቅ ዐዋጅ ነው። ይህ ረቂቅ ዐዋጅ ረቂቅ ዐዋጅ ከጅምሩ የተለያየ ተቃውሞ ገጥሞታል ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎችም አስነስቷል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የዛሬውን የጥያቄው መልስ ዝግጅት ያዘጋጀችው ጽዮን ግርማ ሁለት እንግዶችን አወያይታለች።ተወያዮቹ፤ በአሁኑ ሰዓት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካን የተፈጠሮ ሙዚየም የጥናት ቡድን አባል ናቸው። በሞያቸው ደግሞ የጥንታዊ ቅርስ ተመራማሪ ናቸው። ቀደም ባለው የኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢትዮጵያ የባሕል ሚኒስቴር ውስጥ ተመራማሪ ነበሩ።

ሁለተኛው ተወያይ ዶ/ር ብርሃን መስቀል አበበ ሰኚ ናቸው። በዋሽንግተን ዲሲ የሕግ የፖሊሲና የቢስነስ አማካሪ ናቸው። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነበሩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የሕግ አማካሪ ነበሩ። በኒዩርክ የተባበሩት መንግሥትታ ዲፕሎማት ሆነው ሠርተዋል።

እንግዶቹ ከአድማጭ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ በመስጠት ውይይት አድርገዋል። ያወያየቻቸው ጽዮን ግርማ ነች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG