ዋሺንግተን ዲሲ —
በካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት ከተቃጠሉ ቤቶች ውስጥ በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት፣ የአደጋ አስወጋጅ ሠራተኞች አነፍናፊ ውሾችን እየተጠቀሙ መሆናቸው ተገለፀ።
ሰሜን ካሊፎርኒያ ውስጥ የደረሰው ይኸው ሰደድ እሳት፣ ካለው እሑድ ጀምሮ እስካሁን በተረጋገጠው መሠረት፣ የ31 ሰዎች ሕይወት ያጠፋ ሲሆን፣ መሞት መዳናቸው ካልታወቀው ወደ 9መቶ ከሚሆኑት ሰዎች ውስጥ ምን የተሰማ ወይም የታወቀ ነገር አለመኖሩም ተዘግቧል።
የሰኖማ አውራጃ ፖሊስ ሮበርት ጊኦርዳኖ እንዳስረዱት፣ የተቃጠሉትን ሰዎች ማንነት ለማወቅ ፈፁሞ አዳጋች ነው።
“የገሚሶቹ አካላት እንዳለ ተሟልቶ ቢገኝም ያንዳንዶቹ ግን ብትንትን ብሎ ከአመድ በቀር ምንም መለየት አይቻልም” ብለዋል ፖሊሱ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ