በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል


ዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ክፍለ ሀገር ካሊፎርኒያ በበርካታ ስፍራዎች ሲነድ በሰነበተው ሰደድ እሳት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ክፍለ ሀገር ካሊፎርኒያ በበርካታ ስፍራዎች ሲነድ በሰነበተው ሰደድ እሳት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል።
ደረቅ እና ንፋሳማ በሆነው የአየር ሁኔታ ምክንያት ቃጠሎው እስከነገ ማክሰኞ ድረስ እንደሚቀጥል የአየር ሁኔታ ትንበያ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ከክፍለ ሃገርዋ ዋና ከተማ ከሳክራሜንቶ በስተሰሜን ካምፕ ፋይር ላይ እየተዛመተ ያለውንና እስካሁን ቢያንስ ሃያ ዘጠኝ ሰዎች የገደለውን ቃጠሎ ለመቆጣጠር በሺዎች የተቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ተሰማርተዋል። እስካሁን ያልተገኙ ሁለት መቶ ሃያ ስምንት ሰዎች መኖራቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።
የእሳት አደጋ ባለሥልጣናቱ እንደገለጡት ሰደድ እሳቱን ሃያ አምስት ከመቶ ያህሉን ለመቆጣጠር ተችሏል። በካሊፎርኒያ ታሪክ ከምንጊዜውም የከፋ መሆኑ የሚነገርለት ይህ ቃጠሎ ስድስትስ ሺህ ስድስት መቶ ህንጻዎችን አውድሟል።
ከዚያ በስተምሥራቅ ከምትገኘው እና ዘጠና ሶስት ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት አጎራባችዋ ቺኮ ከተማ እሳቱ በሰዓት ሃምሳ ስድስት ኪሎ ሜትር ፍጥነት በሚነጉደው ንፋስ እየገሰገሰ በመሆኑ ነዋሪዎቹ ለቅቀው እንዲወጡ ታዘዋል። በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ቃጠሎው ሁለት ሰዎች ገድሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG