በሰደድ እሳት የተጎዳው ካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ ዝናብ እና ንፋስን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል ለተባለው ጎርፍ በመዘጋጀት ላይ ነች፡፡ የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የነፍስ አድን ዋናተኞች ጎርፉን ለመከላከል ነዋሪዎች አሸዋ የተሞሉ ጆንያዎች እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኦሬገኗ ፖርትላንድ ከተማ አውራ ጎዳናዎቿን ብዛት ያለው የግግር በረዶ መከላከያ አልብሳለች፡፡ በተጨማሪም የኦሪገን እና አይዳሆ ግዛት ባለሥልጣናት ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ ለሚመጣ የበረዶ እና የበረዶ ውሽንፍር ለመዘጋጀት የአደጋ ጊዜ መጠለያዎችን አዘጋጅተዋል። የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ደቡባዊ ካሊፎርኒያ በተራሮች ላይ እስከ ስድስት ኢንች ዝናብ፤ እንዲሁም በባህር ዳርቻ አካባቢዎች እና ሸለቆዎች ደግሞ ዝናብ በብዛት ሊጥል እንደሚችል ተንብየዋል፡፡ ዝናቡ ኃይለኛ ዛፎችን ሊጥል እና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሊያስከትል የሚችል እንደሚኾን ስጋት አለ።
መድረክ / ፎረም