ዋሺንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮችን የመዘገበች የመጀመሪያ ክፍለ ሃገር ሆናለች።
አርባ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉዋት ምዕራባዊዋ ክፍለ ግዛት እስከዛሬ ማክሰኞ የተረጋገጠው የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር ሦስት ሚሊዮን አስራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አራት ደርሷል። ከዚህ ውስጥ ሠላሳ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አራት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኮሮናቫይረስ በተያያዘ ከአውሮፓ እና ከብራዚል በሚገቡ ተጓዦች ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ ገደብ ከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ እንዲነሳ ያደረጉትን ውሳኔ የተረካቢው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እንደሚቀለብሰው አስታውቋል።