በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት የሞተው ሰው ብዛት ቢያንስ አርባ ሁለት ደረሰ

ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜናው ካሊፎርኒያ ሲነድ ይሰነበተው ሰደድ እሳት የገደለው ሰው ብዛት ቢያንስ አርባ ሁለት ደረሰ። በክፍለ ሃገሩዋ ታሪክ ከደረሱት ሁሉ ባጠፋው የሰው ህይወት ብዛት የከፋው ሆኗል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜናው ካሊፎርኒያ ሲነድ ይሰነበተው ሰደድ እሳት የገደለው ሰው ብዛት ቢያንስ አርባ ሁለት ደረሰ። በክፍለ ሃገሩዋ ታሪክ ከደረሱት ሁሉ ባጠፋው የሰው ህይወት ብዛት የከፋው ሆኗል።

ፓራዳይዝ የምትባለውን ከተማ ለአራት ቀናት በተከታታይ ባዳረሳት ሰደድ እሳት ምክንያት እስካሁን ያልተገኙ በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች እንዳሉ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

ደቡባዊ ካሊፎርኒያ ውስጥ የደረሱት ቃጠሎውች ደግሞ ሁለት ሰዎችን ገድለዋል።

የካሊፎርኒያ አገረ ገዢ ጄሪ ብራውን አስቸኳይ ጊዜ ያወጁ ሲሆን የገንዘብ ዕርዳታም ጠይቀዋል።

ትናንት ሰኞ ማታ የካሊፎርኒያውን የሰደድ እሳት “ከባድ አደጋ” ብለው የገለጹት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በቃጠሎው ለተጎዱ መርጃ የሚሆን ገንዘብ ከፌዴራል መንግኅት ወጪ እንዲደረግ ፈቅደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG