በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በሰብልና አትክልቶች የደረሰው ጉዳት የዋጋ ንረት ማስከተሉ ተነገረ


በኢትዮጵያ ለበርካታ ሣምንታት የዘለቀ ውርጭ በሰብልና አትክልቶች ያደረሰው ጉዳት የዋጋ ንረት አስከተለ፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ ወደ 7.8 ከመቶ ከፍ ማለቱን ገልፆ፤ ሁኔታውንም ከአትክልትና ምግብ ዋጋ ንረት ጋር አያይዞታል። ይህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከፍተኛው ግሽበት ሆኗል።

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ ወደ 7.8 ከመቶ ከፍ ማለቱን ገልፆ፤ ሁኔታውንም ከአትክልትና ምግብ ዋጋ ንረት ጋር አያይዞታል። ይህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከፍተኛው ግሽበት ሆኗል።

ወትሮ፤ የዋጋ ንረት የሚገለፀው፤ “እንደጨው አልቀመስ አለ” እየተባለ ነበር! ዘንድሮ፤ ጨው እራሱ አልቀመስ ብሏል። በጨው በረንዳ በጅምላ አራት ብር ተሰጥቶ መልስም ይገኘው የነበረው፤ አሁን በእጥፍ ጨምሯል።

ከንግድ ሚንስቴር ባገኘንው መረጃ መሠረት ጨው ብቻ ሳይሆን፤ ለመንግሥት ሰራተኞች የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ከጥር 1 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ሲሆን፤ የዋጋ ንረት ተከትሏል።

በዚህም የነዳጅና የመጓጓዣ እንዲሁም የሸቀጦች ዋጋ አሻቅበዋል።

የንግድ ምንስቴር ቃል አቀባይ ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስረዱት ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ምንም አይነት ምክንያት ሳይኖራቸው እንዳይጨምሩ ግንዛቤ ለመፍጠርና በአንጻሩ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎችን ለማስተካከል ቅጣት መጣሉን ገልጸዋል።

በእርግጥ፤ በምጣኔ ሀብት ሁሉም ነገር የአቅርቦትና የፍላጎት ሆኖ በገበያ የሚመራ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ገበያ ስርዓት የደላሎችና የመንግስት እጅ ረጂም መሆኑ ይታወቃል።

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ ወደ 7.8 ከመቶ ከፍ ማለቱን ገልጾ፤ ሁኔታውንም ከአትክልትና ምግብ ዋጋ ንረት ጋር አያይዞታል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፍተኛው የሆነውን ግሽበት እንዳስከተለ ከግብርናና ንግድ ምንስቴር የተሰጡ መግልጫዎች ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ የፈጠረው ውርጭ ለበርካታ ሳምንታት መዝለቁን ያስረዳል። የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ መስሪያቤት የአየር ሁኔታው ከዜሮ በታች የወረደባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን አብራርቶ አሁን ያለው ሁኔታ ግን የተሻለ ነው ይላል። ምክትል ስራ አስኪያጁ አቶ ዱላ ሻንቆን አነጋግሬያለሁ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በኢትዮጵያ በሰብልና አትክልቶች የደረሰው ጉዳት የዋጋ ንረት ማስከተሉ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG