በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሴኔጋል በርካታ ሰዎች በመኪና አደጋ በመሞታቸው ብሔራዊ የሃዘን ቀን ታውጇል


ሴኔጋል ካፍሪን ከተማ ትናንት እሁድ ሁለት አውቶብሶች ተጋጭተው 38 ሠዎች ከሞቱ
ሴኔጋል ካፍሪን ከተማ ትናንት እሁድ ሁለት አውቶብሶች ተጋጭተው 38 ሠዎች ከሞቱ

በሴኔጋል ትናንት እሁድ ሁለት አውቶብሶች ተጋጭተው 38 ሠዎች ከሞቱና 80 የሚሆኑት ደግሞ ከቆሰሉ በኋላ በአገሪቱ የሦስት ቀናት ሃዘን ታውጇል።

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልን ጨምሮ ሌሎችም ባለሥልጣናት ባወጡት መግለጫ ትናንት እሁድ ማለዳ ላይ ከመዲናዋ ዳካር 137 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ካፍሪን ከተማ ሁለት አውቶብሶች መጋጨታቸውን አስታውቀዋል።

በአገሪቱ የቅርብ ግዜ ታሪክ ዘግናኙ አደጋ ነው ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው በትዊተር አስታውቀዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ሃዘንም አውጀዋል።

አንድ የአካባቢው አቃቤ ህግ እንዳሉት አደጋው ሊከሰት የቻለው የአንደኛው አውቶብስ ጎማ ሲፈነዳ መንገዱን በመሳቱ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረው አውቶብስ ጋር ተላትሟል።

ለረዥም ዘመን ያገለገሉ፣ አሮጌና ከልክ በላይ የተጫኑ ትላልቅ አውቶብሶችና ዕቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በአውራ ኦዳናዎች ላይ በፍጥነት ስለሚበሩ በሴኔጋል የመኪና አደጋ በብዛት ይስተዋላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኬያ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰ የአውቶብስ አደጋ 20 ሰዎች ሲሞቱ 49 ደግሞ ጉዳት ደርሶባልቸዋል።

ከኡጋንዳ ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው አውቶብስ ኬንያ ድንበር ውስጥ ከገባ በኋላ አደጋው መድረሱ እንደታወቀ የኤኤፍፒ ሪፖርት አመልክቷል።

የአደጋው ምክንያት ከልክ በላይ ፍጥነት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG