በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውቶብስ ውስጥ በፈነዳ ቦምብ 18 የሦሪያ ወታደሮች ተገደሉ


ሦሪያ
ሦሪያ

ሦሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ውስጥ ትናንት ሀሙስ አንድ አውቶብስ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 18 የሦሪያ ወታደሮች ሲገደሉ ሌሎች 27 መቁሰላቸውን ወታደራዊ ምንጮችን የጠቀሱት የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡


ሦሪያ ውስጥ ውጊያው እንደገና እያገረሸ መሆኑንም የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡


ባላፈው መጋቢት በማዕከላዊ ሦሪያ ፓልሚራ አቅራቢያ አማጽያኑ በወታደራዊ አውቶብስ ላይ ባደረሱት ተመሳሳይ አደጋ 13 ወታደሮችን ሲገድሉ 18 የሚሆኑትን ማቁሰላቸው ተነገሯል፡፡


የሦሪያ ባለሥልጣናት ለእንደዚህ ያሉ ጥቃቶች ተጠያቂዎቹ በደቡብና ማዕከላዊ ሪያ የሚንቀሳቀሱ የእስላማዊ መንግሥት አማጽያን ቡድኖች ናቸው ይላሉ፡፡


አማጽያኑ እአአ ከ2019 ጀምሮ ይቆጣጠሯቸው የነበሩትን በርካታ አካባቢዎች ቢያጡም አሁን ድረስ ሦሪያ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ተመልክቷል፡፡


ትናንት ሀሙስ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ባካሄዱት ውጊያ፣ እአአ ከ2018 ጀምሮ በቱርክ በሚደገፉ ተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር የነበረችውን አፍሪን ከተማ መያዛቸው ተመልከቷል፡፡

XS
SM
MD
LG