በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ከሁለት ዓመታት በኋላ ምርጫ አልወዳደርም አሉ


ፎቶ ፋይል፡- የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፔር እንኩሩንዚዛ
ፎቶ ፋይል፡- የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፔር እንኩሩንዚዛ

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፔር እንኩሩንዚዛ ከሁለት ዓመታት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አልወዳደርም በማለት አስታውቀዋል።

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፔር እንኩሩንዚዛ ከሁለት ዓመታት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አልወዳደርም በማለት አስታውቀዋል። ይህን ያልታሰበ ውሳኔ ዛሬ ያሰሙት እአአ እስከ 2034 ድረስ ስለጣን ላይ ሊያቆያቸው የሚችል የህገ-መንግሥት ለውጥ እንዲደረግ ከገፉ ከሦስት ሳምንታት በላይ የሆነ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው።

ፕሬዚዳንት እንኩሩንዚዛ የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶችም ጭምር ባሉበት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስዎች በተገኙበት ባደረጉት ንግግር “ውክልናችን በ2020 ነው የሚያበቃው” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኪሩንዱ ባደረጉት ንግግር ከሦስት ዓመታት በፊት ቃለ መሃላ በፈፀሙበት ወቅት ለሌላ የሥልጣን ጊዜ ለመቆየት እንደማይሞከሩ ቃል ገብተው እንደነብር ህዝቡን አስታውሰዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚመረጠውን ፕሬዚዳንት ባለኝ አቅም ሁሉ ለመርዳት ዝግጁ ነኝ ሲሉም አስገንዝበዋል።

“አዲሱ ህገ መንግሥት ጠላቶቻችን እንደሚሉት ለፕየር እንኩሩንዚዛ በሚያመች መንገድ የተቀየሰ አይደለም” ብለዋል የ54 ዓመት ዕድሜው ፕሬዚዳንት።

ከሦስት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫ መጀመርያ ላይ የተሰየምኩት በምክር ቤት እንጂ በምርጫ ስላሆነ አይቆጠርም በማለት ለሦስተኛ ጊዜ በሥልጣን የመቆየት አላማ እንዳላቸው በገለፁበት ወቅት ሀገሪቱ ከባድ የፖለቲካ ቀውስ ገጥሟት እንደነበር የሚታወቅ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG