በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡሩንዲ ከዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት በመውጣት የመጀመሪያ ሀገር

ቡሩንዲ ከዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ በመውጣት የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች። ቡሩንዲ ፍርድ ቤቱ በአፍሪካ ላይ ከልክ ያለፍ ትኩረት ስለሚያደርግ እወጣለሁ ብላ ካስታወቀች ዓመት ሆኗታል።

ቡሩንዲ ከዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ በመውጣት የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች። ቡሩንዲ ፍርድ ቤቱ በአፍሪካ ላይ ከልክ ያለፍ ትኩረት ስለሚያደርግ እወጣለሁ ብላ ካስታወቀች ዓመት ሆኗታል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቡሩንዲ ዕርምጃ ላይ ፈጥኖ በሰጠው ምላሽ ቡሩንዲ ከፍርድ ቤቱ መውጣትዋ በሀገርዋ በስፋት የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ለመብት ረጋጣ ሰለባዎች ፍትህ ለመስጠት ካለባት ኃላፊነት ነፃ አያደርጋትም ብሉዋል።

ቡሩንዲ ከአባልነት በመውጣት የፍርድ ቤቱን ሥራዎች ለማስቆም ብትሞክርም ፍርድ የመጀመሪያ ምርመራዎቹን መቀጠል ይችላል ያለው አምነስቲ የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒየር ኑኩሩዚዛ መንግሥት አልተባበርም ቢል እንኳን አይሲሲ ወንጀሎቹን የሚመረምርበት እና ተጠያቂዎቹን ለፍርድ የሚያቀርብበት መንገድ አለው ሲል አስገንዝቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG