በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡሩንዲ የጋዜጠኞች ሥነ ምግባር ሕጓን አሻሻለች


የቡሩንዲ መንግሥት ከሥነ ምግባር በተያያዘ ውንጀላ የሚቀርብባቸው ጋዜጠኞች ላይ የእስራት ቅጣት መጣል የሚከለክል ሕግ በቅርቡ አጸደቀ።

በአዲሱ ሕግ የሙያ ሥነ ምግባር አጓድለዋል ተብለው የሚበየንባቸው ጋዜጠኞች እስራት ሳይሆን ከ350 እስከ 525 ዶላር የገንዘብ መቀጮ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል።

አብዛኞቹ የቡሩንዲ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አዲሱን ሕግ በደስታ የተቀበሉ ሲሆን እንዳንዶች ቅሬታ አሰምተዋል።

"የቡሩንዲ መንግሥት የፕሬስ ነጻነትን ከልቡ ማክበር ከፈለገ የአስር ዓመት እስራት ቅጣት ተፈርዶባት ወህኒ ቤት የምትገኘውን የራዲዮ ዝግጅት አቅራቢ እና ተንታኝ ፍሎሬን ኢራንጋቢዬን ይልቀቃት" በማለት የሚጠይቁም አሉ።

የሚዲያ ሕጉን በፕሬዚደንት ኤቫራስቴ ኢንዲሲሚዬ ሊቀ መንበርነት የተመራው ካቢኔ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG