በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ ፓርላማ ሀገሪቱ ከዓለምአቅፉ የወንጀል ችሎት አባልነት እንድትወጣ ወሰነ


የቡሩንዲ ፓርላማ አባላት
የቡሩንዲ ፓርላማ አባላት

የቡሩንዲ ሕግ አርቃቂዎች፥ ሀገሪቱ ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት አባልነቷ እንድትወጣ በከፍተኛ ድምፅ ወስነዋል።

የቡሩንዲ ሕግ አርቃቂዎች፥ ሃገሪቱ ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት አባልነቷ እንድትወጣ በከፍተኛ ድምፅ ወስነዋል።

ፕሬዘዳንቱ በሕጉ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።

አንዳንድ የቡሩንዲ ፓርላማ አባላት ግን፥ እርምጃው ሀገሪቱን በአደገኛ ሁኔታ ከቀረው ዓለም እንድትገለል ያደርጋታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፥ መንግሥቱ የተባበሩት መንግሥታትና ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ቡድኖችን መመሪያዎች መጣሱ የሚያመለክተው፥ በዚያች ሃገር ውስጥ ገለልተኛ የፖሊስ ኃይል አስፈላጊ መሆኑን ነው ብለዋል።

ሙሐመድ የሱፍ ያጠናቀረው ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የቡሩንዲ ፓርላማ ሀገሪቱ ከዓለምአቅፉ የወንጀል ችሎት አባል እንድትወጣ ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:44 0:00

XS
SM
MD
LG