በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡርኪና ፋሶ የፈረንሳይ ቴሌቭዥን ጣቢያ ሥርጭቶችን አገደች


የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት "ፍራንስ 24" የተባለው የፈረንሳይ መንግሥት ቴሌቭዥን ጣቢያ ሥርጭቶችን አገደ፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያው ከሰሜን አፍሪካ የአል ቃይዳ ቅርንጫፍ መሪ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ካስተላለፈ መታገዱ ታውቋል።

የቡርኪና ፋሶ የጦር ሠራዊት ባለፈው ጥቅምት ወር መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ ሥልጣን ከያዘ ወዲህ የፓሪስ እና የዋጋዱጉ ግንኙነት በእጅጉ እየሻከረ ሄዷል። ባለፈው ጥር ወር ፈረንሳይ ወታደሮቿን በአንድ ወር ውስጥ እንድታስወጣ ቡርኪና ፋሶ ማዘዟ ይታወሳል፡፡

ፍራንስ 24 ቴሌቭዢን ጣቢያ እና ራሱን “የእስላማዊ ማግረብ አልቃይዳ ኤሚር” ብሎ ከሚጠራው ከዬዚድ ሜባረክ ጋር ያካሄደውን ቃለ መጠይቅ በቅርቡ አስተላልፏል፡፡

የቡርኪና ፋሶ ኮምዩኒኬሽንስ ሚንስትር ዣን ኢማኑዌል ኡዋድሬጎ ባወጡት መግለጫ “የፈረንሳዩ የቴሌቭዥን ጣቢያ ቃለ መጠይቁን በማስተላለፉ የነዚህ ሽብርተኞች አፈ ቀላጤ ሆኖ ማገልገሉ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይ ለሽብር ድርጊቶቻቸው እና ለጥላቻ ንግግራቸው ሕጋዊ መድረክ ሰጥቷል” ሲሉ ከሰዋል፡፡

ወጪው በፈረንሳይ መንግሥት የሚሸፈነው ፍራንስ 24 በበኩሉ “ መሠረተ ቢስ ውንጀላ” ብሎታል፡፡

XS
SM
MD
LG