በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ ሳን መሠረት ባደርገ ጥቃት 28 ተገደሉ - የመብት ተሟጋች ቡድን


አቶ ዳውዳ ዲያሎ
አቶ ዳውዳ ዲያሎ

የቡርኪና ፋሶን ሠራዊት የሚደግፉ የሚሊሺያ ቡድኖች ፉላኒ በተባሉት የጎሳ አባላት ላይ በፈጸሙት ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ 28 ሠዎች ተገድለዋል ሲል አንድ የመብት ተሟጋች ቡድን ዛሬ ከሷል።

ኑና በምትባለው ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ፉላኒ የተባሉና በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን የጎሳ አባላት ኢላማ ያደረገ ነው ሲሉ የመብት ስብስብ ቡድን ዋና ጸሐፊ ዳውዳ ዲያሎ ተናግረዋል።

የፉላኒ ጎሳ አባላት ኢላማ የተደረጉት በአገሪቱ ለዓመታት ሁከትን ሲፈጽሙ ቆይተዋል የሚባሉትን የእስልምና አክራሪዎች ይደግፋሉ በሚል መሆንኑ የአሶሲዬትድ ዘገባ አመልክቷል።

በኑና የተፈጸመው ጥቃት በቅርቡ በጂሃዲስቶች ለተፈጸመ ጥቃት በቀል ነው ሲሉ የሰብዓዊ ቡድኑ ጸሃፊ ጨምረው አስታውቀዋል።

የቡርኪና ፋሶ መንግሥት በ28 ሰዎች ግድያ ጉዳይ ላይ ምርመራ መጀመሩንና፣ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ጥሪ አቅርቧል።

ከአል-ቃይዳ እና ኢስላሚክ ስቴት ጋር ግኑኝነት አላቸው የሚባሉ አክራሪ ቡድኖች ባለፉት 7 ዓመታት በፈጸሙት ጥቃት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድሉ፣ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑትን ደግሞ አፈናቅለዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።

እክራሪ ህይሎቹን መንግስት ያስወግዳል የሚል እምነት ባለመኖሩም በቡርኪና ፋሶ ሁለት መፈንቅለ-መንግሥቶች ባለፈው ዓመት ተካሂደዋል።

በፉላኒ ጎሳ ላይ የሚፈጸመው ሁከት ባለፉት ሦስት ወራት በአዲሱ ሁንታ መሪ ሻለቃ ኢብራሂም ተራኦሬ አገዛዝ መጨመሩንና፣ 250 የሚሆኑ ሕገ-ወጥ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሰባዊ መብት ቡድኑ አመልክቷል።

የጂሃዲስቶችን ጥቃት ለመከላከል በሚል መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ በጎፈቃደኛ ሚሊሺያዎችን ለሠራዊቱ ድጋፍ እንዲሰጡ መልምሏል።

XS
SM
MD
LG