የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማኅበረሰባዊና የሃይማኖት ቡድኖችና የፀጥታው ኃይል ተወካዮች የሀገሪቱን ድህረ መፈንቅለ መንግሥት አቅጣጫ በሚመለከት ንግግር ጀምረዋል፡፡
300 የሚሆኑት እነዚህ ተወካዮች የተሰበሰቡት በዘጠኝ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሁለተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረባት በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ መሆኑ ተነገሯል፡፡
የብሄራዊ ጉባኤው ተወካዮች አዲስ የሽግግር ፕሬዚዳንት እንደሚመርጡ ተገልጿል፡፡
በመፈንቅለ መንግሥቱ ሥልጣኑን የጨበጡት ወታደራዊ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንትነቱን እሳቸው እንዲወስዱት ቢጠይቁም ቦታውን እንደማይፈልጉት መናገራቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡
ትራኦሬ በስብሰባው ላይ አለመካፈላቸውን የተነገረ ሲሆን፣ ለጉባኤ አባላት በላኩት መልዕክት “ልዩነታችንን ወደ ጎን ማድረግ ይገባናል... ሙሉ ተስፋ የተሞላበትንም አዲስ ምዕራፍ መጻፍ አለብን” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡