በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ተጨማሪ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ወደ ቡርኪና ፋሶ እንደምትልክ አስታወቀች


የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቡርኪና ፋሶ
የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቡርኪና ፋሶ

ሩሲያ ወደ ቡርኪና ፋሶ ተጨማሪ ወታደሮችን እንደምትልክ በምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አስታውቀዋል።

ከዩክሬን ወረራ ወዲህ ከምዕራቡ ዓለም ጋራ ያላት ግንኙነት የሻከረው ሩሲያ፣ በአፍሪካ ተጽእኖዋን ለመጨመር በመጣር ላይ ነች፡፡

በአህጉሪቱ የሚገኙ የሩሲያ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ቁጥር እንደምትጨምርና በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ የሩሲያ ተወካዮችን እንደምታሰለጥንም ላቭሮቭ ዋገዱጉ ውስጥ ተናግረዋል።

ትላንት ማክሰኞ ቡርኪና ፋሶ የገቡት ላቭሮቭ፣ ከወታደራዊ አገዛዝ መሪው ካፕቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ጋራ ተነጋግረዋል። የትራኦሬ ወደ ሥልጣን መምጣት ግንኙነታቸውን እንዳጎለበተው ላቭሮቭ ጨምረው አስታውቀዋል።

በእ.አ.አ መስከረም 2022 በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የቡርኪና አፋሶ ወታደራዊ መሪዎች፣ የፈረንሣይ ወታደሮችን እና ዲፕሎማቶችን ከሃገሪቱ አባረው፣ ለወታደራዊ እገዛ ፊታቸውን ወደ ሩሲያ አዙረዋል።

ከአል ቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግስት ጋራ የወገኑ እስላማዊ ነውጠኞች በእ.አ.አ 2015 በቡርኪና ፋሶ ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 2ሚሊዮን የሚሆኑ ደግሞ ተፈናቅለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG