በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪናፋሶ የወርቅ ማዕድን በደረሰ ፍንዳታ ከ50 በላይ ሰዎች ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ቡርኪናፋሶ አቅራቢያ የሚገኘው የማዕድን ማውጫ ቦታ
ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ቡርኪናፋሶ አቅራቢያ የሚገኘው የማዕድን ማውጫ ቦታ

በደቡብ ምዕራብ ቡርኪናፋሶ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ስፍራ አጠገብ በደረሰ ፍንዳታ 59 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ100 በላይ ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ብሄራዊ የዜና አገልግሎት እና የዐይን ምስክሮች አስታወቁ።

ፍንዳታው የደረሰው ጂቦምብሎራ በተሰኘው ሲሆን፣ የፍንዳታው መንስኤ የወርቅ ማዕድንን ለማጥራት በሥራ ላይ የሚውል ኬሚካል ክምችት እንደሆነ ተነግሯል።

"በሁሉም ስፍራ አስክሬኖችን አይቻለሁ ፣በእጅጉ አሰቃቂ ነበር!”፣ ብለዋል ሳንሳን ካምባዎ የተባሉ በፍንዳታው ወቅት በስፍራው የነበሩ ደን ጠባቂ ለአሶሼትድ ፕረስ በስልክ ሲያስረዱ።

የመጀመሪያው ፍንዳታ የተከሰተው ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ሲሆን ፣ ሌሎች ፍንዳታዎች መከሰታቸውን ተከትሎ ሰዎች ከአካባቢው የእግሬ አውጭኝ ሽሽት እንደ ጀመሩ የዐይን ምስክሩ አክለዋል።

ቡርኪናፋሶ በወርቅ ምርት ከፍተኛ ዕድገት እያሳዩ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ስትሆን ፣ በአሁኑ ወቅት ከአህጉሩ በብዛት ወርቅ በማምረት 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የሀገሪቱ ዋነኛ ወደ ውጭ ሀገራት የሚላክ ምርትም ሆኗል። ዘርፉ ለ1.5 ሚሊየን ሀገሪቱን ህዝብ የቀጠረ ሲሆን፣ በ2019 የአውሮጳዊያኑ ዓመት የነበረው የኢኮኖሚ ዋጋው 2 ቢሊየን ዶላር ነበር።

XS
SM
MD
LG