በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሣይ ዲፕሎማቶችን አባረረች


ፎቶ ፋይል፡- የቡርኪና ፋሶ ካርታ
ፎቶ ፋይል፡- የቡርኪና ፋሶ ካርታ

ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሣይ ዲፕሎማቶችን “በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል” በሚል ከሃገሯ አባራለች፡፡ የኤኤፍፒ ዚና ወኪል ተመልክቼዋለሁ ያለውንና ከሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፈረንሣይ ኤምባሲ የተላከውን ደብዳቤ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሦስቱ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር እንዲወጡ ታዘዋል።

ርምጃው፤ በቀድሞ ቀኝ ገዢዋ እና በአፍሪካዊቷ ሃገር መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ማሳያ ነው ተብሏል። በፓሪስ የሚገኘው የፈረንሣይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቶቹን መባረር በተመለከተ ወዲያውኑ አስተያየት አልሰጠም።

በመስከረም ወር 2014 ዓ/ም በካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የተመራው ሁንታ፣ በቡርኪና ፋሶ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ ወዲህ፣ እስከ እ.አ.አ 1960 ድረስ ቅኝ ገዢዋ ከነበረችው ፈረንሣይ ጋራ ሃገሪቱ ያላት ግንኙነት ሻክሯል።

ሁንታው ሥልጣን ከያዘ ወዲህ፣ የፈረንሣይን አምባሳደር ከሃገሪቱ ሲያስወጣ፣ ከእ.አ.አ 1961 ጀምሮ የነበረውን ወታደራዊ ስምምነት ሽሯል። የፈረንሣይ ወታደሮች ከሃገሪቱ እንዲወጡ በማድረግ፣ ለፀጥታ ጥበቃ እገዛ ለማግኘት ፊቱን ወደ ሩሲያ አዙሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG