በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡርኪና ፋሶ ጠ/ሚ ሥልጣናቸውን ለቀቁ መንግሥት ጫና በዝቶበታል


ፎቶ ፋይል፦ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ማርክ ክርስቲያን
ፎቶ ፋይል፦ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ማርክ ክርስቲያን

የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ማርክ ክርስቲያን ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው በለቀቁት የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳቢያ በጂሃዲስቶቹ አማጽያን ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት እየበረታባቸው መሆኑ ተነገረ፡፡

በቡርኪና ፋሶ ጅሃድስቶን ለማጥፋት ስድስት ዓመት በቆየው ዘመቻ ወደ ሁለት ሺ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

አመጹ እየበረታ መጥቶ ትናንት ሀሙስ 13 የቡርኪና ፋሶ በጎ ፈቃድ ሰላም አሰከባሪዎች በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ህይወታቸውን ማጣታቸውን አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በየቀኑ ቤተሰቦቻቸውን የሚቀብሩ ዜጎች እየበዙ በመምጣታቸው እየፈጠረ በመጣው ህዝባዊ ቁጣ ጠቅላይ ምኒስትሩ ጆሴፍ ማሬ ዳብሬ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ አስገድዷቸዋል፡፡

በቡርኪና ፋሶ አዲስ የሚመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ችግር ለማስወገድ በጅሃድስቶቹ ላይ ጠንክራ እርምጃ የሚወሱድ መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል የሚለው ግፊትም እያየለ መምጣቱ ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG