ቡርጂ ወረዳ ሶየመ ከተማ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 20 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገለፁ።
ቅዳሜ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም አካባቢውን ከሚያጎራብቱ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እና ከሌሎች የደቡብ ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየመ ከተማ ውስጥ ለገበያ የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ጥቃት መከፈቱን አስተዳዳሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።
ዘገባው የገልሞ ዳዊት ነው።