በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመን ፓርላማ ኮሚቴ ኢትዮጵያዊያን አስረጂዎች


የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ዲርክ ኒበል ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት
የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ዲርክ ኒበል ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት

ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ለጀርመን ፓርላማ የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ በሰጡት ማብራሪያ ላይ የተካሄደ ቃለ-ምልልስ

በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ሚስተር ዲርክ ኒበል የተመራ አንድ የጀርመን መንግሥት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርጎ ወደ ሃገሩ መመለሱና ያንን ጉብኝት ተከትሎ የጀርመን ፓርላማ የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በርሊን ላይ ገለፃዎችን አዳምጦ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የጀርመን መንግሥት ልዑካን ቡድን አባል ሆነው የሄዱት የጀርመኑ ፓርላማ አባልና የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር ሚስተር ቲሎ ሆፐ ባለፈው ሣምንት የተካሄደውንም የኮሚቴውን የኢትዮጵያ ጉዳይ ማብራሪያ ስብሰባ መርተዋል፡፡

የእንደራሴው ቲሎ ሆፐ ፅ/ቤትም ሰሞኑን አንድ የፕሬስ መግለጫ አውጥቶ በትኗል፡፡ መግለጫው በመግቢያው ላይ ባሉ ሁለት መሥመሮች እንዲህ ይላል፡- “የዴሞክራሲን እጦትና የሰብዓዊ መብቶችን መረገጥ ክእንግዲህ ለማስተናገድ የማይሹቱ ድምፆች ይበልጥ እያስተጋቡ የሄዱት በዐረቡ ዓለም ብቻ አይደለም፤ ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም እየተከሰተ ነው፡፡”

የጀርመን ቡንደስታግ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሪዎችና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጋር ተገናኝቶ የተነጋገረ ሲሀን ኮሚቴው ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሰዎችና የመብቶች ተሟጋቾች አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ መከልከሉን፣ ሥርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተጠሪዎች እንደሚታሠሩ ያስረዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

የጀርመን መንግሥትም ከኢትዮጵያ ጋር ወደኢኮኖሚ ልማት ትብብር ድርድሮች ሲገባ እነዚህን አሣሣቢ ያሏቸውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ እንዲያስገባ የሚስተር ቲሎ ሆፐ ፅ/ቤት የፕሬስ መግለጫ እንደሚያሳስብ በዚህ ዝግጅት የመጀመሪያ ክፍል መገለፁ ይታወሣል፡፡

በዚህ የጀመርን ፓርላማ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በአስረጂነት ከቀረቡትና በአስተባባሪነትም ከተሣፉት መካከል የተቃዋሚ መሪዎቹ ዶ/ር መረራ ጉዲናና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ እንዲሁም በአውሮፓ ከሚገኙ የሰብዐዊ መብቶች ተሟጋቾች ወ/ሮ አሣየሽ ታምሩና አቶ ስዩም ሃብተማርያም ይገኙበታል፡፡ የአስረጂዎቹን አስተያየት፤ ያነጋገራቸው ሰሎሞን አባተ ውይይቱን ያቀርባል፡፡

ለዝርዝሩ ድምፁን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG