በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋይት ሃውስ ባለሥልጣናት ልማት ተኮር ጉብኝት እያደረጉ ነው


ፎቶ ፋይል፦ በሩዋንዳ ለጤና ጣቢያዎች ከጸሀይ ጨረር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስልጠና ላይ ያሉ ሰራተኞች
ፎቶ ፋይል፦ በሩዋንዳ ለጤና ጣቢያዎች ከጸሀይ ጨረር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስልጠና ላይ ያሉ ሰራተኞች

የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ አየር ንብረት፣ ጤና፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ የጾታ እኩልነት በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ሊከናወኑ የሚችሉ ሃምሳ የሚሆኑ ሥራዎችን ለመለየት በተለያዩ የዓለም ማዕዘናት እየተዘዋወሩ ናቸው።

የዋይት ሃውስ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ምክትል የብሄራዊ ጸጥታ አምካሪ የሆኑት ዳሊፕ ሲንግ “ቢልድ ባክ ቤተር ወርልድ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን መርሃ ግብር ይዘው በቅርቡ ጋናን እና ሴኔጋልን ጎብኝተዋል።

ፕሬዚደንት ባይደን መርሃ ግብሩን ባለፈው ሰኔ በተካሄደው ቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሲያስተዋውቁ በታዳጊ ሃገሮች ከፍተኛ ጥራት እና ግልጽነት ያለው የመሰረተ ልማት አጋርነት ለመፍጠርና በሚያስፈልጉ ወጪዎችም ድጋፍ ለማድረግ ዓላማው ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኤምሊ ሆርን በሰጡት ቃል የዳሊፕ ሲንግ የጋና እና የሴኔጋል ጉብኝት የመርሃ ግብሩ የመጀመሪያ የውይይት ጉዞ መሆኑን ገልጸው ፕሬዚዳንት ባይደን ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ያለንን ትስስር ለማጠናከር እና በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ይበልጡን እየሰፋ የሄደውን የቁሳዊ፣ የዲጂታል እና ሰብዓዊ መሰረተ ልማት ክፍተት ለማጥበብ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG