በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጀርያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እንደቀጠለ ነው


ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደው የናይጀርያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እንደቀጠለ ሆኖ፣ ውጤቱ ተቀራራቢ በመሆኑ ትናንት ዕሑድም የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ክፍት ሆነው መዋላቸው ተገለፀ።

ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደው የናይጀርያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እንደቀጠለ ሆኖ፣ ውጤቱ ተቀራራቢ በመሆኑ ትናንት ዕሑድም የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ክፍት ሆነው መዋላቸው ተገለፀ። ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተካሄደ ግጭት የሟቾች ቁጥርም ወደ 30 ከፍ ማለቱ ታወቀ።

ነፃው የናይጄሪያ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው፣ የቅዳሜው ምርጫ በተጓጎለባቸው በአንዳንድ የሌጎስ የሪቨርስ እና የአናመበራ ስቴቶች፣ ሌላ የምርጫ ቀን ይወስናል።

ወደ አፍሪካ በሚተላለፈው የቪኦኤ እንግሊዝኛ አገልግሎት እንደተገለፀው፣ የናይጄሪያ ምርጫ ቦርድ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ውጤቶችን ይፋ ያደርጋል።

ሁለቱም ዕጩዎች፣ ፕሬዚዳንቱ ሙሐማዱ ቡሃሪ እና ዋናው ተቀናቃኛቸው አቲኩ አቡባካር፣ አሸናፊ መሆናቸውን በየፊናቸው መናገራቸው ይሰማል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG