በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ነሃስ ሜዳሊያ አገኘች


አትሌት ለተሰንበት ግደይ
አትሌት ለተሰንበት ግደይ

ሊጠናቀቅ አንድ ብቻ ቀን በቀረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጨረሻዎቹ ውድደሮች እየተከናወኑ ነው። በኤትሌቲክስ በሴቶች 10ሺ ሜትር ውድድር ተውልደ ኢትዮጵያዊ የኔዘርላንድ ተወዳዳሪ ሲፋን ሀሰን ድል አድርጋለች ።የአሁኑን ውድድር በ29 ደቂቃ ከ55 ሰከንዶች ከ30 ማይክሮ ሰከንዶች ያጠናቀቀችው ሲፋን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ያገኘቻቸውን ሜዳሊያ ብዛት ሶስት አድርሳለች። ቀደም ባሉት በ5ሺ ሜትር ወርቅ፣ በ1500 ሜትር ውድድሮች ደግሞ የነሃስ ሜዳሊያ መሸነፏ ይታወሳል። ሲፋንን በመከተል ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው ሌላው ትውልደ -ኢትዮጵያዊ የባህሬን ተወዳዳሪ ቃልኪዳን ገዛኸኝ ናት። ሶስተኛ ደረጃን በማግኘት ኢትዮጵያን ለነሃስ ሜዳሊያ ያበቃቻት ደግሞ ለተሰንበት ግደይ ሆናለች።

ቀደም ብሎ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኬንያኑ ፔሪዝ ጂፕቺርቺር እና ብርጌድ ኮስጌ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል። ፔሪዝ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ27 ደቂቃ ከ38 ሰከንዶች ወስዶባታል። ሞውሊ ሳይድል ከዩናይትድ ስቴትስ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ሮዛ ደረጀ ከኢትዮጵያ የአራተኛ ደረጃን አግኝታለች።

XS
SM
MD
LG