ዋሺንግተን ዲሲ —
የብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣትን አስመልክቶ በሚደረገው ድርድር ብዙም እንቅስቃሴ ባልታየበት በአሁኑ ወቅት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሬዛ መይ ከአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ጋር ሊነጋገሩ ነው።
ለወራት ያህል ሲካሄድ በቆየው ንግግር በብዙ ክፍሎች ላይ ሥምምነት አስገኝቷል። ይሁንና በሰሜን አየርላንድና የአውሮፓ ሕብረት አባል በሆነችው አየርላንድ መካከል ያለውን የድንበር አያያዝን የአካተቱ አብይት መሰናክሎች አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትርዋ ከአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ሌሎቹ 27 የአውሮፓ ሃገራት መሪዎች የብሪታንያን መውጥት በሚመለከት ስለሚደረገው ድርድር እራትት ላይ ይወያያሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ