በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ዶኔትስክ ላይ እንደገና ጥቃት ልትከፍት እየሞከረች መሆኗ ተገለጠ


የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ
የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ

የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲ ሬዝኒኮቭ " ጦርነት ውስጥም ሆነን የለውጥ ዕርምጃችን ይቀጥላል" ሲሉ ተናገሩ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ሲሆን የመንግሥት ባለሥልጣናት በተከታታይ ሥራቸውን እየለቀቁ አለያም እየተባረሩ ባሉበት እና እሳቸውም ከቦታቸው ይነሳሉ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት መሆኑ ነው።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ወደሌላ ቦታ ይዛወራሉ በማለት የተናገሩት አንድ የፓርላማ አባል ሲሆኑ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በዚህ ጉዳይ በይፋ አስተያየት አልሰጡም። ትናንት ዜሌንስኪ በሰጡት ቃል"ወታደራዊ ተሞክሮ ያላቸውን ኃላፊዎች መሾምን ጨምሮ አስተዳደራችንን ለማጠናከር በመስራት ላይ ነን" ብለዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሥራቸውን የመልቀቅ ሃሳብ እንደሌላቸው ገልጸው የሚሆነውን የሚወስኑት ፕሬዚዳንቱ ናቸው ብለዋል።

ባለፈው ጥር ወር የዩክሬን ኃይሎች የአቅርቦቶች ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት ምክትል የመከላከያ ሚንስትር ቪያቼስላቭ ሻፖቫሎቭ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኅፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ትናንት ሰኞ በሰጡት ቃል የዩክሬይኑ ጦርነት እየተባባሰ ከሄደ ዓለማችን ወደተስፋፋ ጦርነት ማምራቷ ነው የሚል ሥጋት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ጉተሬዥ ይህን ያሉት በኒው ዮርክ ለዲፕሎማቶች ባደረጉት ንግግር ሲሆን "በዕንቅልፍ ልባችን ሳይሆን ዐይናችንን ገልጠን ወደተስፋፋ ጦርነት እያመራን መሆናችን ያስፈራኛል" ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጠዋል።

XS
SM
MD
LG