በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያው የመድሃኒት ኩባኒያ አስትራ ዜኔካ የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባቱ


የብሪታንያው የመድሃኒት ኩባኒያ አስትራ ዜኔካ የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባቱ ማምረቱ ሂደት ላይ የተፈጠረውን ስህተት በተመለከተ ከመንግሥት ተቆጣጣሪዎች ጋር ተባብሮ ምርመራ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ።

የመድሃኒት ኩባኒያው እና ኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ክትባቱ ሙሉው ምጥን ብልቃጥ ለሰው ሲሰጥ ከሚያሳየው ውጤት ይልቅ ቀነስ ተደርጎ ሲሰጥ የተሻለ እንደሚያመጣ ማመናቸው የአስትራ ዚኔካ ቃል አቀባይ ገልጿል።

የኩባኒያው ዋና ሥራ አስፈጻሚም በክትባቱ ላይ ተጨማሪ ዓለምቀፍ ሙከራ ማድረግ ማስፈለጉ እንደማይቀር ጠቁሟል።

አስትራ ዜኔካ በዚሁ የአውሮፓ 2020 ውስጥ አራት ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባቶችን ሊያቀርብ ማቀዱ ሲታወቅ፣ ከዚያ በፊት የተወሰነ ሊያከፋፍል እየተዘጋጀ ባለበት ነው ይህ የአመራረት እክል የተከሰተው።

XS
SM
MD
LG