በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልዑል ፊሊፕ አረፉ


ልዑል ፊሊፕ
ልዑል ፊሊፕ

ልዑል ፊሊፕ በተወለዱ በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ዛሬ አርብ ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት አስታውቋል።

"ግርማዊት ንግሥት ኤልዛቤት የተወዳጁን ባለቤታቸውን የኤዲንብረ መስፍን ልዑል ፊሊፕን ማረፍ በጥልቅ ኃዘን ይፋ ያደርጋሉ " ሲል ከቤተ መንግሥቱ የወጣው መግለጫ አስታውቋል። ልዑሉ ዛሬ ጠዋት በዊንዘር ቤተመንግሥት ማረፋቸውን መግለጫው አመልክቷል።

ልዑሉ በቅርቡ በልብ ህመማቸው ምክንያት ለበርካታ ሳምንታት ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ እንደቆዩና በለንደን በሚገኘው የሴንት ባርቶሎሜው ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረገላቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG