የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ መይ ባለፈው ሚያዝያ ወር ባደረጉት ጥሪ መሠረት ዛሬ በሀገሪቱ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት ስለ ምትወጣበት ጉዳይ ድርድር በሚካሄደበት ወቅት ጠንካራ ውክልና እንዲኖራቸው ነው ምርጫው እንዲካሄድ ጥሪ ያደረጉት።
ይሁንና የብሪታንያው ዋና ተቃዋሚ ድርጅት የሆነው ሌበር ፓርቲ ክፍተቱን እየሞላ በመሆኑ በከፍተኛ ድምፅ የማሸነፋቸው ጉዳይ እየደበዘዘ ነው።
የምርጫው ዘመቻ በተከታታይ በተካሄዱት የአሸባሪዎች ጥቃቶች ምክንያት ትኩረቱ ደብዝዟል ሲል ዘጋብያችን ሄነሪ ራይዌል ከለንደን በላከው ዘገባ ጠቅሷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ