በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእንግሊዝ ዘረኝነትን የሚቃወሙ ሰልፍ ወጡ


ፀረ ስደተኛ ተቃውሞ ሰልፎች፣ በሊቨርፑል፣ ብሪታንያ
ፀረ ስደተኛ ተቃውሞ ሰልፎች፣ በሊቨርፑል፣ ብሪታንያ

በእንግሊዝ ለበርካታ ቀናት ሲካሄድ የነበረውን የቀኝ አክራሪዎች ፀረ ስደተኛ ሰልፎችና ጥቃቶች በመቃወም በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል።

ዘረኝነትን በመቃወም በበርካታ ከተሞች የወጡት ሰልፈኞች የቀኝ አክራሪዎቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ መንገዶችን እና ሌሎችንም ቦታዎች ተቆጣጥረው ውለዋል።

የቀኝ አክራሪዎቹ ስደተኞችን በመቃወም ባደረሱት ጥቃት ከሳምንት በፊት ሶስት ሕፃናት ተገድለዋል።

ፀረ ፋሺስት ሰልፈኞቹ ከቀኝ አክራሪዎቹ የበለጠ ቁጥር የነበራቸው በመሆኑ፣ ቀኝ አክራሪዎቹ አንድ መቶ በሚጠጉ ከተሞች ጠርተውት የነበረው ሰልፍ መደረግ እንዳይችል አድርገዋል።

ስድስት ሺሕ የሚሆኑ ልዩ የፖሊስ አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ለተከሰተው ቀውስ ፖሊስ “ኢንግሊሽ ዲፌንስ ሊግ” የተሰኘውንና የነውጠኛ እግር ኳስ ደጋፊዎችና እስልምና ጠሎች ድርጅት አባላትና መሪዎች ተጠያቂ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG