በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዝ አምባሳደርና ፕሬዚዳንት ትረምፕ ጉዳይ


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በዩናይትድ ስቴትስ የእንግሊዝ አምባሳደር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “እርባና ቢስ”፣ “በራስ መተማመን የጎደላቸው” እና “ብቃት የሌላቸው”፤ አስተዳደራቸውም “በተለየ ሁኔታ የተመሣቀለ” እንደሆነ በመግለፅ ማዋደቃቸው ይፋ ከወጣ በኋላ ከአምባሳደሩ ጋር “ከእንግዲህ እንደማይሠሩ” ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለእንግሊዝ ኤምባሲ ኦፊሴላዊ ደብዳቤ ስለመላክ አለመላኩ ለጊዜው አይታወቅም። ፕሬዚዳንት ትረምፕ ባወጡት የትዊተር መልዕክት ግን ዲፕሎማት ኪም ዳሮችን እንደማያውቋቸው፣ ዲፕሎማቱ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተወደዱ ወይም በመልካም የሚታዩ ሰው አለመሆናቸውን ገልፀዋል።

እንግሊዛዊያኑ ግን አምባሳደር ዳሮች ወደ ሃገራቸው የሰደዱትን ዲፕሎማሲያዊ ጦማር አስሻልኮ ያወጣው ማን እንደሆነ ለማወቅ እየማሰኑ ናቸው።

“ነገሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ማግኘት አለብን” ያሉት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀረሚ ኸንት መልዕክቱ የትና እንዴት እንደሾለከ ያወቁ ጊዜ ግን መዘዙ ብርቱ እንደሚሆን አስገንዝበዋል።

ዋሺንግተን የሚገኙት የእንግሊዝ የንግድ ሚኒስትር ሊያም ፎክስም በጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዚዳንቱ ልጅና አማካሪ ኢቫንካ ትረምፕ ጋር ሲገናኙ “ይቅርታ” እንደሚሉ ተናግረዋል።

የአምባሳደሩ መልዕክት የታሰበው ለእንግሊዝ ከፍተኛ ሚኒስትሮችና የመንግሥት ሠራተኞች በመሆኑ “ሹክ” ባዩም እዚያው የሎንዶን ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት መካከል ያለ እንጂ ከውጭ መግሥት የሚጠረጠር አለመሆኑን ባለሥልጣናቱ ያምናሉ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእንግሊዝ አምባሳደርና ፕሬዚዳንት ትረምፕ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG