በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ የኮቪድ-19 ገደቦችን ሙሉ በሙሉ ልታነሳ ነው


የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ ከነገ በስትያ ጀምሮ ኮቪድ-19ን በተመለከተ በሀገሪቱ ውስጥ የተጣሉ ገደቦች እንደሚነሱ ይፋ አደረጉ። በዚህም መሰረት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን የማግለል ግዴታ የለባቸውም።

በሀገሪቱ ፓርላማ ንግግር ያደረጉት ጆንሰን፣ ሀገራቸው አሁንም ቢሆን ዜጎች እስከ አውሮፓዊያኑ ሚያዚያ አንድ ድረስ እንዲመረመሩ፣ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች፣ ደግሞ በቤታቸው እንዲቆይ እንደምታበረታታ አስታውቀዋል። ዜጎች ግላዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ከተጠቀሰው ቀን በኃላ እንግሊዝ ለዜጎቿ ኮቪድ ምርመራ እንደማትከፍል ይፋ ተደርጓል። ጆንሰን በንግግራቸው ከሰሞኑ ቫይረሱ ለተገኘባቸው ንግሥስት ኤልሳቤጥ ቀዳማዊት መልካም ጤና ተመኝተው፣ የሳቸው በኮቪድ-19 መያዝ ወረርሽኙ እንዳላበቃላት ማሳያ መሆኑን ጠቋሚ መሆኑን አውስተዋል።

XS
SM
MD
LG