በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ብሪታንያ በአስትራዜኔካ ኩባኒያ የተሰራውን የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት ዛሬ ጀምራለች፥ የኩላሊት እጥበት ታካሚ የሆኖ የሰማኒያ ሁለት ዓመት አረጋዊ ይህን ክትባት ለመከተብ የመጀመሪያ ሆነዋል። ግማሽ ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ይሄኛው ክትባት በፋይዘር ባዮንቴክ ከተቀመመው ክትባት ዋጋው ረከስ እንደሚል ደግሞም እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ባለው ማቀዝቀዣ መቀመጥ ያለበት ባለመሆኑ ለማጓጓዣ ቀለል ያለ መሆኑ ተገልጿል።

የፋይዘሩ ክትባት ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለበርካታ የጤና ባለሙያዎች ሲሰጥ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት ብሪታንያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በተለይም ለወጥ ያለው እና ሳይንቲስቶች ከፊተኛው ይበልጥ ተላላፊ ነው ያሉት አዲሱ ዓይነት ቫይረስ ስርጭት እያሻቀበ መሆኑ ታውቋል።

ግሪክም አዲሱ ዓይነት ቫይረስ ከወደብሪታንያ በመጡ ሰዎች በኩል ገብቶብኛል ስትል ትናንት አስታውቃለች።

ህንድ በአስታራዜኔካ የተሰራውን ክትባት በአጣዳፊ ሁኔታ መስጠት እንዲጀመር ፈቅዳለች። በሀገሯ የተሰራው ክትባትም ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅዳለች። አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ህንድ ለስራችው ክትባት ፈቃዱ ተቻኩሎ ተሰጥቷል የሚል ስጋት አሰምተዋል።

XS
SM
MD
LG