በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴቪድ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ


የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን
የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን

የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን፣ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው ተሹመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ፣ ያልተጠበቀውን ሹመት የሰጡት፣ ከፍተኛ የሥልጣን ወንበሮችን ዳግም እያዋቀሩ ባሉበት ወቅት ነው።

የ57 ዓመቱ ዴቪድ ካሜሮን፣ እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2016 እንግሊዝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ካገለገሉ በኋላ፣ አገሪቱ ከአውሮፓ ኅብረት አባልነት ለመልቀቀ ያደረገችውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ ከሥልጣን ለቀዋል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ እንድትቆይ ካሜሮን ወትውተው ነበር።

ዴቪድ ካሜሮን፣ ያለፉትን ሰባት ዓመታት፣ የሕይወት ታሪካቸውን በመጻፍ እና በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው አሳልፈዋል። ግሪንሲል ካፒታል የተሰኘው የፋይናንስ ኩባንያቸው ግን ስኬታማ ሳይኾን ቀርቷል።

ካሜሮን፣ ከሦስት ዓመታት በፊት፣ የመንግሥት ሚኒስትሮች ለኩባንያቸውን ሥራ እንዲያመቻቹላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቋቸው በመገኘታቸው፣ የቀድሞ ባለሥልጣናት በመንግሥት ፖሊሲ ላይ ተጽእኗቸው እስከ ምን ድረስ መኾን አለበት፤ የሚል ጥያቄ አሥነስቷል።

ንጉሥ ቻርለስ፣ የላይኛው ወይም የመኳንንቱ ሸንጎ አባል ያደረጓቸው ዴቪድ ካሜሮን፣ የፓርላማ አባል ኾነው ባይመረጡም የሚኒስትርነት ሥልጣን እንዲይዙ እንዳስቻላቸው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG