አዲሱ የእንግሊዝ የሠራተኛ ፓርቲው መንግስት የጋመውን የእንግሊዝ ፖለቲካና የኑሮ ውድነት ቀውሱን እንደሚያረጋጋ አስታውቋል።
ዛሬ በከፍተኛ ድምቀት በተከፈተው ፓርላማ ላይም አዲሱ መንግስት “የብሔራዊ ተሃድሶ” ያለውን ዕቅድ ይፋ አድርጓል።
ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ፣ በመንግስት የተዘጋጀውን እና የእንግሊዝን የገንዘብ ቀውስ ለማረጋጋት እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት ያለመውን ሕግ በዝርዝር የያዘውን ሰነድ በንባብ አሰምተዋል።
ተጨማሪ መኖሪያ ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች እንደሚገነባ እንዲሁም የሠራተኞችን መብት ለማጠናከር እና አዲስ የኢንዱስትሪ ልማት ስልት ለመፍጠር እንደሚሠራ አዲሱ መንግስት አስታውቋል።
በእንግሊዝ የወግ አጥባቂ ፓርቲው መንግስት በነበረበት ባለፉት 14 ዓመታት የተከሰተውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግርን ለማስወገድ ለውጥ እንዲደረግ ጉጉት ያደረባቸው ድምፅ ሰጪዎች፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተደረገው ምርጫ፣ የሠራተኛ ፓርቲው በከፍተኛ ድምፅ እንዲያሸንፍ አድርገዋል።
የገንዘብ ሥርዓቱን ማረጋጋትና የኢኮኖሚ ብልጽግና መፍጠር የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ዋና ትኩረት እንደሆነም ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም