በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት


ትናንት ብሪታንያ ለህዝቧ በስፋት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በመስጠት የመጀመሪያዋ የምዕራብ ሃገር የመሆኗን የትናንቱን ዜና ተከትሎ ዛሬ ደግሞ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ቻይና ሰራሹ ክትባት ሰማኒያ ከመቶ ውጤታማነት ማሳየቷን ተናገረች።

የኤሚሬትስ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሳይኖፋርም የተባለው የቻይና መንግሥት የመድሃኒት ድርጅት በቀመመው የኮቪድ ክትባት ሙከራ ተሳትፈናል ብሏል፤ ክትባቱ በአጣዳፊ ሁኔታ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ባለፈው መስከረም ፈቃድ መስጠቱንም አመልክቷል።

ክትባቱ የከፋ የጎን ጠንቅ ስጋት አላሰየም ቢልም ስለሙከራው ውጤት በዝርዝር አላብራራም::

ሆኖም ውጤታማነቱ የክትባት ዘመቻ ለመጀመርና ኢኮኖሚውንም ለመክፈት አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል ብሏል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩናይትድ ሴቲትሱ የመድሃኒት ኩባንያ ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮንቲክ የተቀመመው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ላይ ባደረገው ግምገማ ክትባቱ በከፍተኛ ደረጃ አዋጭ ሆኖ እንዳገኘው እና በተከተቡ ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት እንዳልፈጠረ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG