በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ስለምትወጣበት መንገድ ሥምምነት


የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕረዚዳንት ጃን ክላውድ ጃንከር
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕረዚዳንት ጃን ክላውድ ጃንከር

የብሪታንያና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ስለምትወጣበት መንገድ ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን “ትልቅ ሥምምነት ነው” ብለዋታል። የሀገሪቱ መንግሥት በሌሎች ቅድሚያ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ሲባል የብሪታንያ ምክር ቤት የሀገሪቱን ከአውሮፓ ህብረት መዋጣት በመጪው ቅዳሜ ማከናወን አለበት ሲሉ በትዊተር አስገንዝበዋል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕረዚዳንት ጃን ክላውድ ጃንከር በበኩላቸው ዛሬ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት “ፋላጎት ካለ ሥምምነት ይኖራል። ዛሬ አሸንፈናል” ብለዋል። ሁለቱም ወገኖች ከሦስት ዓመታ በላይ ለሆነ ጊዜ ሲነታረኩ ከቆይ በኋላ ነው ዛሬ ሥምምነት ላይ ሊደርሱ ያቻሉት።

ሥምምነቱ ለአውሮፕ ህብረትና ለብሪታንያ “ፍትሃዊና ሚዛናዊና ነው” ብለዋል ጃንከር። 27 ቱ የአውሮፓ ሀገሮች መሪዎች ዛሬ ብራሰልስ ሲሰባሰቡ እንዲያፀድቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሪታንያ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት እንደምትወጣ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG