ዋሺንግተን ዲሲ —
ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት፣ ከሦስት ዓመታት በፊት በህዝበ-ውሳኔ በወሰነችው መስረት፣ ምርጫ ማካሄዱ፣ ለረዥም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን የፍች ሂደት፣ ፍጻሜ እንዲያገኝ ያስችል ይሆናል የሚል ግምት አለ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የምርጫ ዘመቻ ትኩረት፣ “የብሪታንያ መውጣት ይጠናቀቅ” የሚል ነው። ወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው በምክር ቤቱ፣ የብዙሃንነት ቦታ ሲይገኘ፣ የብሪታንይ ፍቺ ፣ እስከ መጪው ጥር ወር ማብቂያ ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ለመግፋት እንደሚያስችላቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ዋናው ተገዳዳርያቸው የሌበር ፓርቲ መሪ ጀረሚ ኮርባይን፣ ካሸንፍኩ የብሪታንያ ህዝብ አሁንም 28 አባል ሃገሮች ካሉት የአውሮፓ ህብረት፣ መውጣት ይፈልግ እንደሆነ ለማረጋገጥ፣ አዲስ ህዝብ-ውሳኔ እንዲካሄድ አደርጋለሁ ብለዋል።
የምርጫው ኦፊሴላዊ ውጤት ነገ እንደሚታወቅ ተገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ